ስለ አፍሪ ስካንዲክ
አፍሪ ስካንዲክ በስካንዲናቪያን  እና በእንግሊዝ  እንዲሁም በመላው ዩናይትድ  ኪንግደም ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው  በአይነቱ በስካንዲናቪያን  ውስጥ  የመጀመርያ የሆነ በተለያዩ የአፍሪካዊያን መግባቢያ ቋንቋወች በኢንተርኔት (በኮምፒይተርም ሆነ በሞባይል )  ድህረ ገፅ ላይ ግለስቦችም ሆኖ የንግድ ድርጅቶች ምርትና አገልግሎቶቻቸውን ሊያስተዋውቁ የሚችሉበት ማንኛወም ሰው ለሽያጭም ሆነ ለኪራይ ለማቅረብ የሚፈልገውን  ነገር የሚያስተዋውቅበት ማንኛወም ሰው የንግድ ድርጅቶቹን በድህር ገፁ ላይ በመመዝገብ ማስተዋውቅ የሚችልበት እንዲሁም የተለያዩ አይነት ዝግጅቶችን ማስተዋውቅ የሚቻልበት ዘርፈ ብዙ የሆኑ የማስታወቂያ አይነቶችን ማለትም እንደ መኪናወች ፤ ኤሌክትሮኒክሱች ፤ ኮምፒዩተሮች ፤ ሞባይሎች ፤የኢንዱስትሪ እቃዎች ፤ ንብረቶች ፤ የቤት እቃዎች እና የተለያዩ አይነት የአማካሪነት እና ሌሎች የአገልግሎት ማስታወቂያወችንም ሁሉ ያካተተ ድህር ገፅ እና የንግድ ማስታወቂያ ኢንፎርሜሽን የማግኛ (የመረጃ) ቋት ነው ::

እንደሚታውቀው የሳካንዲናቪያን አገሮች በተለይም ስዊድን ለብዙ አፍሪካዊያን ሁለተኛ መኖርያ አገራቸው እየሆነች መምጣቱ ይታውቃል:: የ2016  የስዊድን መንግስት ማእከላዊ ስታቲስቲክ መሰርያ ቤት የህዝብ ቁጥር እድገት መረጃ እንደሚያሳየው በስዊድን ነዋሪ የሆነው የአፍሪካዊያኖች ቆጥር 194,758 ደርሶል ::  ይህ የመረጃ አሃዝ ከስዊድን ውጭ ተወለደው ወደ ስዊድን በመግባት ነዋሪ የሆኖትን አፍሪካዊያን ነው እንጂ በስዊድን ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ከአፍሪካዊያን ወላጆችም ሆነ ከአፍሪካዊያን እና ከስዊድናዊያን ወይም ከአፍሪካዊያን እና ከሌሎች በስዊድን  ውስጥ ከሚኖሮ ዜጎች የተውለዱትን ትውልድ አፍሪካዊያንን አይጨመርም :

በመሆኖም ከዚህ መረጃ መረዳት የሚቻለው በስዊድን ውስጥ ሊኖር የሚችለው አፍሪካዊ ከላይ ከተጠቀሰወም ቁጥር እጅግ የበዛ መሆኖን ነው:: በዚህ መልኩ ከግዜ ወደ ግዜ በፍጥነት እየጨመር የመጣው የአፍሪካዊያን ነዋሪወች ቁጥር እና  እንዲሁም በስዊድን እና በአፍሪካ አገሮች መካከል ያለው ዘረፈ ብዙ ግንኙነት በጣም እያደገ መምጣቱ ለአፍሪስካንዲክ መመስረት ዋንኞቹ  ምክንያቶች ሆነዋል :: ስለዚህ አፍሪስካንዲክ በአፍሪካዊያን ቋንቋዎች ማለትም በአረብኛ በአማርኛ በሶማሊኛ እና በትግርኛ እንዲሁም አፍሪካዊያኖች በሰፊው በሚጠቀሙበት የአፍሪካ ቋንቋዎች ማለትም  በእንግሊዝኛ እና  በፈረንሳይኛ  ለደንበኞቹ አገልግሎት ለመስጠት መርጧል ::

ይህን ከዚህ ቀደም  በስካንዲናቪያን ያልነበረን በአይነቱ የመጀመርያ የሆነ በተለያዩ የአፍሪካዊያን መግባቢያ ቋንቋወች  የሚሰራ የኢንተርኔት  ማስታወቂያ ማውጫ  የሆነውን የአፍሪ ስካንዲክን ድህረ ገፅ በመጠቀም ማስታወቂያወትን በመላው ስዊድን ፤ በመላው ስካንዲናቪያን አውሮፓ እና ከዛም ባለፍ በአፍሪካ  እና ሌላም አገሮች  ሊገኙ ለሚችሉ ማስታወቂያውት ሊጠቀማቸው ለሚችሉ ሁሉ እንዲዳረስ ያድርጉ ::

( ለግለሰብም ሆነ ለንግድ ደርጅቶች ማስታወቂያ ለማውጣት የምናስከፍለው ዋጋ 85 የስዊድሽ ክራውን ብቻ ነው ቫትንም (Moms) ጨምሮ ።

በተጨማሪ ደግሞ የንግድ ድርጅት ያላችሁ የንግድ ደርጅታችሁን (የኩባንያወቻችሁን ) ስም እና ተዛማጅ መረጃወች የንግድ ማውጫችን ላይ በማውጣት ህዝብ ስለ ንግዳችሁ እንዲያውቅ  ለማድርግ ለምትፈልጉ ሁሉ ለግዜው ምንም ገንዘብ ስለማናስከፍል ይህንን ጥሩ አጋጣሚ ይጠቀሙብት::

በተጨማሪ በአፍሪ ስካንዲክ በየግዜው የሚወጡ የተለያዮ ማስታወቂያወችን ይከታተሉ ::